Fana: At a Speed of Life!

በነዳጅ ቦቴ ሲጓጓዝ የነበረ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነዳጅ ቦቴ ሲጓጓዝ የነበረ ግምቱ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሆነ የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ በሕግ የተከለከለ ልባሽ ጨርቅ በቁጥጥር ስር የዋለው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ (3) 63528 ኢት እና የተሳቢው ቁጥር ኮድ (3) 17794 ኢት በሆነ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ መኪና ውስጥ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ በአዳባ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ መሆኑ ተገልጿል።
በጽህፈት ቤቱ የሕግ ተገዢነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዴሳ ለማ እንደገለጹት÷ ዕቃው የተገኘበት ቦቴ ተሽከርካሪ መነሻውን ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ አድርጎ ወደ መሀል ሀገር እየተጓዘ ነበር።
ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመተው የኮንትሮባንድ ዕቃ ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ የተያዘው ዛሬ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አሽከርካሪውም በቁጥጥር ስር ውሎ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ህብረተሰቡ መሰል ህገ ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት በንቃት በመከታተልና ለሚመለከተው አካል በመጠቆም የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበትም አቶ ኢዴሳ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.