Fana: At a Speed of Life!

በፈረንሣይ በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ የዙር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት በፈረንሣይ ሌቪን በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ የዙር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በሴቶች 3000 ሜትር ዳዊት ስዩም አንደኛ ደረጃን በመያዝና 8:23.24 በሆነ ሰዓት በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማስመዝገብ ጭምር አሸንፋለች፡፡ በዚሁ ውድድር እጅጋየሁ ታዬ ሁለተኛ፣ ፋንቱ ወርቁ ሦስተኛ፣ ወርቅውሃ ጌታቸው አምስተኛ፣ ዘርፌ ውንድማገኝ ሰባተኛ እንዲሁም አያል ዳኛቸው ስምንተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
በወንዶች የ3000 ሜትር ውድድር ለሜቻ ግርማ አንደኛ፣ ሰለሞን ባረጋ ሁለተኛ፣ ጌትነት ዋለ ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር ግርማ ድሪባ ስምተኛ እንዲሁም ንብረት መላክ 13ኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በተመሳሳይ በሴቶች አንድ ማይል ጉዳፍ ፀጋዬ አንደኛ፣ አክሱማይት እምባዬ ሁለተኛ፣ ሂሩት መሸሻ ሦስተኛ፣ ነፃነት ደስታ አራተኛ፣ ወዛም ተስፋይ ዘጠነኛ እንዲሁም ትዕግስት ከተማ 11ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡
በሌላ በኩል በወንዶች 2000 ሜትር ሳሙኤል ዘለቀ አንደኛ፣ ሀ/ማርያም ተገኝ 10ኛ፣ ቶሎሳ ቦደና 11ኛ፣ አብርሃም ስሜ 14ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
በወንዶች 1500 ሜትር ሳሙኤል ተፈራ ሁለተኛ እና አድሃና ካሳዬ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.