Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዘመነና ዜጎቿ የሚኮሩበት የባህር ሀይል ለመገንባት እየሰራች መሆኑን ተገንዝበናል – የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ሃይል ልዑክ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ሃይል ልዑክ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኘ፡፡
የሩሲያ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያለው ሲሆን፥ የዚህም ጉብኝት ዓላማ የዚሁ ትብብር አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ሃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት÷ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባህር ሃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ፥ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የዛሬ ሶስት አመት በአዋጅ መቋቋሙን ገልፀው፥ ክፍሉን በተማረ የሰው ሃይል ለማደራጀት ሥራዎች እየተሰሩ ያሉ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡
ከሌሎች ሀገሮች የባህር ሃይሎች አደረጃጀትና ቀደም ሲል ከነበረ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ልምድ በመውሰድ የተሰጠንን ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ሰርተን በመከላከያ ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷልም ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ ከባህር ሃይሏ ማግኘት የምትችለውን ጥቅምና ግልጋሎት እንድታገኝ ከሩሲያ ፌደረሽን ባህር ሃይል በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ከመከላከያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.