Fana: At a Speed of Life!

የቦረና ፕሮጀክት በ253 ሚሊየን ብር ግንባታው እንደሚጀመር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 205 ሄክታር የሚሸፍነው የቦረና ፕሮጀክት በ253 ሚሊየን ብር ግንባታው እንደሚከናወን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚገነባው የቦረና የከርሰ ምድር ውኃ መስኖ ፕሮጀክት ዙሪያ ከባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የዓለም ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ የከርሰ ምድር ውኃ ፕሮግራም አስተባባሪ ቪክቶር ቫስኩዌዝ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ወንደሰን ፈለቀን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ተገኝተዋል፡፡
ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ ቦረና በተደጋጋሚ በድርቅ እንደሚጠቃ እንዲሁም ከፍተኛ የመልማት ፍላጎት ያለበት አካባቢ መሆኑን ገልጸው÷ በዓለም ባንክ ድጋፍ ለሚከናወነው የቦረና ፕሮጀክት ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በአስቸኳይ ሥራ እንዲጀመር ያደርጋል ብለዋል፡፡
የዓለም ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ የከርሰ ምድር ውኃ ፕሮግራም አስተባባሪ ቪክቶር ቫስኩዌዝ በበኩላቸው÷ የቦረና ፕሮጀክት ለጎረቤት ሀገራት ጭምር ቅርብ በመሆኑ ለአካባቢያዊ ትስስር የፕሮጀክቱ ጠቀሜታ ጉልህ ነው ብለዋል፡፡
የቦረና ፕሮጀክት በአራት ወረዳዎችና በሰባት ክላስተሮች የሚጀመር ሲሆን÷ 205 ሄክታር እንደሚሸፍንም ነው የተመላከተው፡፡ ፕሮጀክቱም በ253 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚከናወን ከሚኒስቴሩ ኮሙኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.