Fana: At a Speed of Life!

በዘንድሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ ንቅናቄ ከ8 ሺህ በላይ ተፋሰሶች ይለማሉ- የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአማካይ ለ20 የሥራ ቀናት በሚቆየው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ ሥራ ከ8 ሺህ 400 የሚልቁ ተፋሰሶች እንደሚለሙ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው ዛሬ በሰሜን ሸዋ ዞን በተካሄደው የተፈጥሮ ሀብት የመስክ ምልከታ ላይ እንደተናገሩት÷ ድህነትን በማሸነፍ በምግብ ራስን ለመቻል የተራቆተውን ምድር ማልማት 2ኛው የህልውና ዘመቻ ነው፡፡

በህወሓት የሽብር ቡድን ተወረው የነበሩ የምሥራቅ ቀጠና አካባቢዎችም በተፈጥሮ ሀብት የልማት ሥራው የተጠናከረ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ከ450 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ያለ የተራቆተ አካባቢ በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት እንደሚለማ የተናገሩት ዶክተር ኃይለማርያም÷ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ህዝብ እንደሚሳተፍም አስታውሰዋል፡፡

በመስክ ምልከታው የተገኙት የአማራ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ በበኩላቸው÷ የህወሓት የጥፋት ኃይልን በመመከት በድህነት መውጫው የተፈጥሮ ሃብት የልማት ስራ ላይ ርብርብ ማድረግ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ በተካሄደው የሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ ምልከታ መርሀ ግብር የ16 ዞኖች ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በታለ ማሞ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.