Fana: At a Speed of Life!

ሁሉም ቤተ እምነቶች የሰላምን አስፈላጊነት ማስተማር ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ቤተ እምነቶች ለተከታዮቻቸው የሰላምን አስፈላጊነት ማስተማር ቀዳሚ ተግባራቸው ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ተናገሩ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ግጭቶች እየተባባሱ ለበርካታ ሰዎች ሞትና ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት ምክንያት መሆናቸውን ያስታወሱት የሃይማኖት አባቶቹ÷ ድርጊቱ በየትኛውም ሃይማኖት የሚወገዝና ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስረድተዋል።
እንዲህ አይነት ድርጊቶች የሚፈፀሙት በምእነትና ማንነት ሰበብ የጥፋት ዓላማ በያዙ ግለሰቦች በመሆኑ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ሊቀበለው እንደማይችል ጠቁመው÷ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ቤተ እምነቶች ለተከታቶቻቸው የሰላምን አስፈላጊነት ማስተማር ቀዳሚ ተግባራቸው ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባት መላዕከ ጸሃይ አባ ወልደብርሃን ገብረ መድህን÷ የሃይማኖት መሪዎች ለሚከተላቸው ህዝብ ምን ጊዜም ሰላምን ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፤ በአንድ አገር ውስጥ ሰላም ከሌለ ሁሉም ነገር የሚበላሽ በመሆኑ ሰላም የምንም ነገር መሰረት መሆኑን ሁላችንም በጥሞና ልንረዳው ይገባል ብለዋል፡፡
በሃይማኖት ሽፋን በህዝብ ዘንድ ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩ አካላትን ማጋለጥ የሁሉም ሃላፊነት ሆኖ መንግስትም በአጥፊዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧ፡፡
በተለይም ወጣቱን ትውልድ በመልካም ስነ ምግባር ከመቅረጽ አኳያ የሃይማኖት አባቶች ትኩረት ሰጥተን ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ያሉት ደግሞ የቃለ-ህይወት ቤተክርስቲያ ቄስ ዶክተር ታረቀኝ ያዕቆብ ናቸው፡፡
ከአዲስ አበባ ነጃሺ መስጂድ ሼህ ሬድዋን ለለምዳ በበኩላቸው÷ በአገር ሰርቶ ለመኖርና በእምነቱ ጸንቶ በመዝለቅ ፈጣሪውን ለማመስገን እንዲችል የሁሉም ዋስትና ሰላም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ሁላችንም በሰላም እንድንኖር የኢትዮጵያ ሰላም የህዝቦች አብሮነት ወሳኝ በመሆኑ የእምነት አባቶች አስተምህሮ ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.