Fana: At a Speed of Life!

ጉዳት የደረሰባቸዉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሙሉ አቅም ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተሠራ ነው- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉዳት የደረሰባቸዉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሙሉ አቅማቸዉ ወደ ሥራ እንዲገቡ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንደገለጹት÷ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ተቋማቱ ዝግጅት አድርገዉ እንዲሰሩ የተለየ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡
የወሎ፣ ወልዲያ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች በህወሓት የሽብር ቡድን በደረሰባቸዉ ከፍተኛ ጉዳት የትምህርት ሥራዉን ሙሉ በሙሉ አቋርጠዉ መቆየታቸዉን አስታውሰው÷ አሁን ላይ ተቋማቱ የጀመሩትን መማር ማስተማር ለመደገፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑንም ነው ያብራሩት፡፡
ተቋማቱን መልሶ ከመገንባት ጎን ለጎን የስነ ልቦና ጥገና ሥራዎች ወሳኝ በመሆኑ÷የስነ ልቦና ባለሙያዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም ሊተባበሩ እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡
አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች በበኩላቸው÷ መምህራን እና ሌሎች የአስተዳደር ሠራተኞች ተማሪዎችን በመደገፍ እያከናወኑት ያለዉ ሥራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው÷የተደረጉ የስነ ልቦና ድጋፎች አወንታዊ ሚና ተጫውተዋል ብለዋ፡፡
በአወል አበራ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.