Fana: At a Speed of Life!

“የዓለም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥምረት” ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሴቶች አባል በመሆን ልምድና እውቀታቸውን በመጋራት ተጠቃሚ የሚሆኑበት የሴቶች ጥምረት ተመሰረተ፡፡
በኢትዮጵያ እና በየትኛውም ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ሴቶችን በአባልነት የሚያካትተው ጥምረቱ ”የዓለም የኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥምረት ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
ጥምረቱ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዳያስፖራ ሴቶች የተመሰረተ ሲሆን÷ እስካሁን በ11 ሀገራት 87 ኢትዮጵያውያን ሴቶች አባል ሆነዋል ፤ 392 የሚደርሱ ደግሞ የአባልነት ፎርም በመሙላት በሂደት ላይ ናቸው ተብሏል።
በኖርዌ የጥምረቱ መስራችና ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ኢትዮጵያ አለማየሁ÷ ጥምረቱ የተለያየ አቅም ያለቸውን ሴቶች በማሰባሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አቅማቸውን አውጥተው ጠንካራ ስራ ለመስራት የሚያስችላቸውን እድል የሚያመቻች ንው፡፡
የአለም የኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥምረት ከባንኮችና ከሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ ሲሆን÷ በኢትዮጵያና በተለያዩ የአረብ አገራት የሚኖሩ ሴቶች ያላቸውን ችሎታ፣ እውቀትና ጉልበት ተጠቅመው የተሻለ ህይወት እንዲመሩ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።
ጥምረቱ በአሁኑ ወቀት ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ የተለያዩ ቢሮዎች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ኢትዮጵያ÷ በጥምረቱ ወላጅ አልባ ሕፃናትን የማሳደግና በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች የመደገፍ ስራ ተጀምሯል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በስዊዲን የጥምረቱ መስራች ወ/ሮ ሳምራዊት ልሳኑ÷ ጥምረቱ ሴቶች በተበታተነ መልኩ የተሰማሩባቸውን መስኮች ወደ አንድ በማምጣት የተደራጀ አካሔድ እንዲከተሉና እንዲደጋገፉ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።
የዓለም የኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥምረት በኢትዮጵያ ፈቃድ አግኝቶ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ በመሆኑ ዓላማውን በመደገፍ ሴቶች ተመዝግበው አባል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.