Fana: At a Speed of Life!

የድርቁ ሁኔታ ያስተለውን ጉዳት ለመቀነስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከቦረና ማህበረሰብ ጎን እንዲቆም የቦረና አባገዳ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድርቁ ሁኔታ ያስተለውን ጉዳት ለመቀነስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከቦረና ማህበረሰብ ጎን እንዲቆም የቦረና አባገዳ ኩራ ጃርሶ ጠየቁ።
አባገዳው የድርቁ ሁኔታ ከዚህ ቀደም ሲከሰቱ ከነበሩት የጠነከረና እያስከተለ ያለውም ጉዳት የከፋ ነው ብለዋል።
አባገዳ ኩራ ጃርሶ የቦረና ማህበረሰብ ከከብቶች ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው መሆኑን አንስተው፥ ድርቁ በከብቶች ላይ ያደረሰው ጉዳት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር እንደዳረገው ገልጸዋል።
እንስሳት በድርቁ እየሞቱ መሆናቸውን አንስተው ወደ ሰው እንዳይሸጋገር ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በእስካሁኑ ሂደት የኢትዮጵያ ህዝብ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፥ ድጋፉ የወገናችንን አለኝታነት ያየንበት ነው ብለዋል።
ሆኖም ከጉዳቱ አንፃር በቂ አለመሆኑን ጠቅሰው፥ መንግስትና ህዝቡ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ነው የጠየቁት።
በአካባቢው ዝናብ ለተከታታይ ወቅቶች ባለመጣሉ ነዋሪዎችን ለምግብ እህል እጥረት የዳረገ ሲሆን፥ የአርብቶ አደሩን ማህበረስ ከብት በከፍተኛ መጠን ለሞት ዳርጓል።
በአፈወርቅ እያዩ እና ታሪኩ ለገሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.