Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ ከተመራ የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ ከተመራውና በሁሉ አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት የክብካቤ ፕሮግራም ላይ ከሚሰራው የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ በሁሉ አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት የክብካቤ ፕሮግራም ላይ ከሚሰራው መቀመጫውን ለንደን ያደረገው በዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ የተመራ የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ቡድን ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል ብለዋል።

ፕሮግራሙ የነገው የሃገራችን ተስፋ ለሆኑት ህፃናት ተገቢውን ክብካቤ በማድረግ በትምህርት ወጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርግና ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ከግብ የሚያድርስ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ይህ የህጻናት ክብካቤ ፕሮግራም የከተማ አስተዳደሩ እና የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ በከተማው ላይ የበጀት ድጋፍና የቅርብ አመራር እየሰጠን የነበረ መሆኑን ያነሱ ሲሆን፥ የታዩትን ውጤቶች ለማስፋፋት በቀጣይ ይህንኑ አጠናክረን በጋራ የምንሰራ ይሆናል ነው ያሉት።

ሙሉ በሙሉ ሲተገበርም ለቀሪ የኢትዮጵያ ክልሎችና ለአፍሪካ አገራትም ጭምር ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ ለፕሮግራሙ ስኬት ድርጅቱ እያደረገ ስላለው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በመዲናዋ 300 ሺህ የሚገመቱ ህፃናት የቅድመ ትምህርት ድጋፍ እንደሚሹ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.