Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሀረሪ ክልል የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የሀረሪ ክልል ርዕሠ መስተዳድር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ሥራ በመጀመሩ የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዛሬ ብርሃን መስጠት በመጀመሩ
የከተማችን ነዋሪዎች፣ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ እንኳን ደስ አለን ብለዋል፡፡
የህዳሴ ግድብ የሚገኝባት ጉባ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ የብርሃን ዘመን ማብሰሪያ ምድር መሆኗንም ገልጸዋል፡፡
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዲሁ ባስተላለፉት የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት÷ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨት በመጀመሩ ኢትዮጵያውያን በአዲስ የብርሃንና የታሪክ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን የሚያበስር ነው ብለዋል፡፡
ይህ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እና የብርሃን ብልጭታም ሀገራችን አሁን ካለባት ውስብስብ ችግር ይልቅ መጪው ጊዜ የኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ብልፅግና እና አንድነት ሀያል መሆኑን የሚያመላክት መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በመሆኑም ከግድቡ ግንባታ ጅማሮ አንስቶ መላው ኢትዮጵያውያን በተለይም የክልሉ ነዋሪ ፕሮጀክቱ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ላደረጉት አስተዋጽኦና ድጋፍ አመሰግነዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.