Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካቶካዊት ቤተክርስቲያን የባሕር ዳርና ደሴ ቅርንጫፍ በጋሸና ከተማ በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የዕለት ምግብ ድጋፍ አደረገች።

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የባሕርና ዳር ደሴ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አባ ስንታየሁ ገላው ባደረጉት ንግግር፥ አሸባሪ ቡድኑ በአማራ እና በአፋር ክልል ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አውግዘው፥ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ለተጎጂ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቤተክርስቲያኗ ድጋፍ እያደረገች ነው ብለዋል።

በጋሸና ከተማ በጦርነት ለተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች 630 ኩንታል ዱቄት እና 4 ሺህ 200 ሊትር የምግብ ዘይት ድጋፍ መደረጉን አባ ስንታየሁ ገልጸዋል።

በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ውድመት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የውሃ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ቤተክርስቲያኗ አቅዳ እየሠራች መሆኑንም ጠቁመዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የከተማው ከንቲባ ሞላ ፀጋው ፥ የከተማው ማኅበረሰብ በአሸባሪው የሀወሓት ወራሪ ቡድን የተፈጸመበት ግፍ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ቤተክርስቲያኗ ላደረገችው የዕለት ምግብ ድጋፍ ምሥጋና ያቀረቡት ከንቲባው ፥ ሌሎች አካላትም መሰል ድጋፎችን እንድያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.