Fana: At a Speed of Life!

በሣምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የአገር አቋራጭ እና የጎዳና ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሣምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ እና እሁድ በተካሄዱ አገር አቋራጭ እና ዓለም አቀፍ የጎዳና ውድድሮች እንዲሁም በስፔን ሲቪላ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በወንዶች አስራር ሃይረዲን 2፡04፡43 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡
በዚሁ ውድድር ፥ አደላድለው ማሞ ሁለተኛ፣ አዱኛ ታከለ አራተኛ፣ አብዲ አሊ ስምንተኛ፣ ረጋሳ ምንዳዬ አስራ ሰባተኛ፣ ኤባ ቱሉ ሰላሳኛ፣ አብዱ እንድሪስ ሰላሳ አምስተኛ እንዲሁም ጌትነት መሌ አርባ አራተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
በተመሳሳይ በሴቶች መገርቱ አለሙ 2፡18፡49 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሆናለች፡፡
በዚሁ ውድድር÷ መሰረት ጎላ 2፡20፡50 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ፣ የሺ ካልአዩ 2፡21፡17 በሆነ ሰዓት በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ጫልቱ ጭምዴሳ አራተኛ፣ ቅድሳን አለማ ስድስተኛ ፣ አዳወርቅ አበርታ ሰባተኛ፣ 15ኛ በላይነሽ ያሚ አስራ አምስተኛ፣ አይናለም ካሳሁን አስራ ስድስተኛ ሆነው ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡
በሌላ በኩል በጉዋዳላጃራ ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች በሱ ሳዶ 1፡09፡12 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸንፋለች፡፡
አትሌት ዳዊት ስዩም የሌቪን 5 ኪ.ሜ ሪከርድን አሻሽላ ከ48 ሰዓታት ባነሰ ቆይታ በ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ተካፍላ 4፡04.35 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሯን በድል ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.