Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እነማን ናቸው?

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበረሰቡ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮችን እንዲጠቁም በማድረግ ከ600 በላይ ዕጩ ኮሚሽነሮች መጠቆማቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ከእነዚህ ውስጥም ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነር ይሆናሉ ያላቸውን 42 ግለሰቦች ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉም ይታወቃል፡፡

ምክር ቤቱ ከማህበረሰቡ የተገኘውን ግብዓት መሰረት በማድርግ መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን 11 ኮሚሽነሮች ሾሟል።

እነርሱም፦

1.መስፍን አርዓያ

የትምህርት ደረጃ: ፒኤችዲ በአእምሮ ህክምና

የስራ ልምድ

ለ6 አመታት በአዲግራት በደሴ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች በሜዲካል ኦፊሰርነት እና በዳይሬክተርነት የሰሩ፤ለ10 አመታት በአማኑኤል ሆስፒታል በሳይካትሪስትነት፤ ለ6 አመታት በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል በፕሮቮስትነት ፤ለ6 አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይካትሪ ዲፓርትመንት ዲን ፣ለ12 አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር ሆነው በዲፓርትመንት ሃላፊ እና ሌክቸለር ሆነው ካገለገሉ በኋላ የሙሉ ፕሮፌሰር ሆነዋል፡፡

ለ11 አመታት ለፌዴራል ሆስፒታሎች የአመራር ቦርድነት፣በአሁኑ ወቅት ከሙያዊ አገልግሎት በተጨማሪ በኢፌዴሪ የማንነት እና አስተዳደር ወሰን ኮሚሽን አባል ሆነው ያገለግላሉ፡፡

2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ

የትምህርት ደረጃ:ከሶርቦን ዩኒቨርስቲ በህግ ማስተርስ ምሩቅ
የስራ ልምድ፡ -ለ2 አመታት በህግና ፍትህ ሚንስቴር የህግ ተንታኝ ባለሙያ፤ ለ2 አመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የአፍሪካ ህብረት የህግ ጥናት ኦፊሰር፤ ለ2 አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ሌክቸረር፤ለ8 አመታት በግል የንግድ ድርጅት ከፍተኛ የህግ አማካሪ፤ ለ4 አመታት አለማቀፍ የህግ አማካሪ በመሆን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ለአለም ባንክ፣ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአማካሪነት ሰርተዋል፤ ለ6 አመታት ለአፍሪካ ሴቶች የሰላም እና ልማት ኮሚቴ ከፍተኛ ኦፊሰር፤ ለ3 አመታት በኦክስፋም አህጉራዊ የሰላም ግንባታ እና የግጭት አመራር አማካሪ፤ ለ14 አመታት በኮንጎ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስጠባቂ ሚሽን ሀላፊ፤ለሳሄል ክፍለ ሀጉር የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ ልዩ መልክተኛ፤ለምእራብ አፍሪካ እና ለሳሄል የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ምክትል ወኪል ሆነው እያገለገሉ ያሉ፡፡

3. ዶ/ር ተገኘወርቅ ጌቱ

የትምህርት ደረጃ
የፒኤች ዲ ድግሪ , በኢኮኖሚክስ፣ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፡ ኒውዮርክ፤ የማስተርስ ዲግሪ በኢኮኖሚክስ፣ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኒውዮርክ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ በልማት አስተዳደር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰርቲፊኬት በአፍሪካ ጥናት፣ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኒውዮርክ

የሥራ ልምድ

ለ40 ዓመታት በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ፣ በመንግሥት አስተዳደር፣ በግጭት አፈታትና አስተዳደር እንዲሁም በልማት ምጣኔ ሀብት ዙሪያ በርካታ ሙያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፤ለ 4 ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ ምክትል ወኪል በመሆን አስተዳድረዋል፤ ለ 3 ዓመታት የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ ምክትል ወኪል በመሆን ያገለገሉ፤ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በተያያዘ ከ65 በላይ አገሮችን በመጎብኘት አገልግለዋል፡፡

በግጭት አፈታት በመልሶ መገንባትና ማቋቋም እንዲሁም የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በመሥራት ሰፊ ልምድ አካብተዋል፣በአሁን ወቅት ከግል ሥራቸው በተጨማሪ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡

4. አምባሳደር ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ

የትምህርት ደረጃ

የፒ.ኤች ዲ ዲግሪ በፍልስፍና፣ ከአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ፣ ኒዘርላንድስ፤ ማስተርስ ዲግሪ በሕግ ከአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ፣ ኒዘርላንድስ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ

የሥራ ልምድ

ለ3 ዓመታት የአፋር ክልል ጠ/ፍርድ ቤት ዳኛ፤ ለ11 ዓመታት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር፤ለ2 ዓመታት በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል መሪ ሪስርቸር፤ ለ3 ዓመታት በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኦማን ሱልጣን አምባሳደር፤ ለ 2 አመታት በቺካጎ ህግና ቢዝነስ ግሩፕ የህግ አማካሪ

5. ወ/ሮ ብሌን ገ/መድህን

የትምህርት ደረጃ

ማስተርስ ዲግሪ በዓለም ዓቀፍ ህግና ሰብዓዊ መብት፤ ከጄኔቫ አካዳሚ ኦፍ Humantiaran and Human Rights እና በዓለም ዓቀፍ ህግ ከግሮኒገን ዩኒቨርስቲ ኔዘርላንድስ፤ ዲግሪ በህግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የሥራ ልምድ

ለ 2 ዓመታት በማስተማር፤ለ 1 ዓመት የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የኢትዮጵያ ቢሮ ሀላፊ፤ ለ 1 ዓመት በዓለም ዓቀፍ ቀይ መስቀል ከፍተኛ የኮሚኒኬሽን ኦፊሰር፤ለ 6 ዓመታት በኒውዚላንድ ኤምባሲ የፖለቲካና የንግድ ጉዳዮች አማካሪ፤ በ 1 ዓመት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአካል ጉዳተኞችናአረጋውያን ዲፓርትመንት ሀላፊ

6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ

የትምህርት ደረጃ – ፒኤችዲ

የስራ ልምድ

ለ2 አመታት የሰላምና ደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ኦፊሰር፤ለ10 አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም አስተባባሪ፤ ከ3 አመታት ጀምሮ የሰላምና ደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ሃላፊ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

7. አቶ ዘገየ አስፋው

የትምህርት ደረጃ: በህግ የማስተርስ ድግሪ
የስራ ልምድ: ለ2 አመታት የህግ አማካሪ እና ጠበቃ፤ለ 2 አመታት የመሬት ይዞታ ሚኒስትር፤
ለ2 አመታት የግብርና ሚኒስትር ፤ለ2 አመታት የፍትህ ሚኒስትር፤ለ2 አመታት የፋኦ አማካሪ፤ በአሁኑ ወቅት የሁንዴ ኦሮሞ ግሬስ ሩት ዴቨሎፕመንት ኢኒሸቲብ ጀኔራል ማናጀር ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

8. አቶ መላኩ ወ/ማሪያም

የትምህርት ደረጃ

የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የሥራ ልምድ

ለ3 ዓመታት የሕግ አማካሪ፤ ለ4 ዓመታት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ፤ለ7 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኮሌጅ እና አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ የትርፍ ሰዓት ሌክቸረር፤ በአሁን ሰዓት የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

9. አምባሳደር መሐሙድ ዲሪር

የትምህርት ደረጃ

ማስተርስ ድግሪ በዓለም አቀፍ ሕግ
የሥራ ልምድ፡በዚምባብዌ እና በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፤በተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ሚኒስትር ሆነው አገልግሎዋል፣በሱማሌና በደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት በኢጋድ ስር ሆነው ያገለገሉ ፤ በሱዳን የሽግግር መንግስት የሰላም ሂደት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የተሽለሙ፤ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የአክሱም ሃውልት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ በተደረገው አገራዊ ሰፊ ጥረት የአስመላሽ ኮሚቴ አባል ሆነው ለተጫወቱት ከፍተኛ ሚና ከመንግሥት ተሽላሚ የነበሩ፤ በአሁን ወቅት በኢስት አፍሪካ ሆልድን የግል ቢዝነስ ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

10. አቶ ሙሉጌታ አጎ

የትምህርት ደረጃ

የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፤ማስተርስ ድግሪ በሕግ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፤

የሥራ ልምድ

ለ 4 ዓመታት በከፋ ዞን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እና ፕሬዚዳንት፤ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት በዋና ሬጅስትራርነት ለአንድ ዓመት የሰሩ፤ በዳኝነት ለሰባት ዓመት የሰሩ፤ ም/ ፕሬዚዳትነት ለሁለት ዓመትና በፕሬዚዳንትነት ለስምንት ዓመት ያገለገሉ፡፡

11. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ

የትምህርት ደረጃ

የመጀመሪያ ዲግሪ በታሪክ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ ማስተርስ ድግሪ በሶሻል አንትሮፖሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ ፒኤችዲ በሶሻል አንትሮፖሎጂ ከ ማርቲን ሉተር ዊተንበርግ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን
ለ 5 ዓመታት የሰላምና ምክክር ጉዳዮች አማካሪ፤ ለ 4 ዓመታት በመምህርነት፤ ለ 2 ዓመታት የፖሊሲ አማካሪና ተመራማሪ ሆነው ያገለገሉ፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.