Fana: At a Speed of Life!

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በህልውና ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ ለመጀመር ዛሬ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።
ከ3ሺህ በላይ የሚሆኑ ነባር ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ ሲሆን÷ ለዚህም ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ ማከናወኑንም ነው የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ አንዳርጌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት።
በህልውና ዘመቻው ምክንያት ለወራት የተቋረጠውን ትምህርት ለማካካስ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር እንደሚሰሩም ነው የገለጹት፡፡
በሳምራዊት የስጋት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.