Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ12 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው 30 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር ውስጥ እስከ የካቲት መጀመሪያ ድረስ ከ12 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው ‘‘ደረሠኝ እሰጣለሁ፣ እቀበላለሁ፣ ህልውናዬን አስከብራለሁ’’ በሚል መሪ ሃሳብ የበጀት ዓመቱን የገቢ ንቅናቄ መድረክ በደሴ ከተማ አዘጋጅቷል፡፡

በመድረኩም ከሁሉም ዞኖች የገቢዎች መምሪያ ኀላፊዎች፣ አስተዳዳሪዎች እና አጋር አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አበበ ገብረ መስቀል ግብር የመንግሥት ዋንኛ የገቢ ምንጭ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ግብርን በወቅቱ አለመክፈል፣ በደረሰኝ አለመሥራት እና የህገወጥ ንግድ መስፋፋት ግብር በተገቢው መንገድ እንዳይሰበሰብ ማነቆዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህንን ለማስተካከል እና የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በቁርጠኝነት መሥራት አለብን ሲሉም መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በበጀት ዓመቱ 30 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ የካቲት መጀመሪያ ድረስ ከ12 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ፀጋ ጥበቡ ገልፀዋል።

ገቢ በመሰብሰብ ሂደቱ ምዕራብ ጎንደር ዞን የእቅዱን 60 ነጥብ 4 በመቶ በመፈፀም ቀዳሚ ሲሆን ፥ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ደግሞ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ተከታዩን ደረጃ ይዟል፡፡

የጎንደር እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደሮች ደግሞ በክልሉ ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ገቢ በመሰብሰብ ሂደቱ አንድ ተቋም ብቻውን ውጤታማ ስለማይሆን ከአጋር አካላት ጋር በጥምረት መሥራት እንደሚያስፈልግ ዶክተር ጸጋ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.