Fana: At a Speed of Life!

ታሪካዊ ምዕራፍን በሚገልጸው የሀገራዊ ምክክር ላይ በኮሚሽነርነት ሀላፊነትን መሸከም ልዩ ክብር አለው – የኮሚሽኑ ሰብሳቢዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ታሪካዊ ምዕራፍን በሚገልጸው የሀገራዊ ምክክር ላይ በኮሚሽነርነት ሀላፊነትን መሸከም ልዩ ክብር አለው ሲሉ የኮሚሽኑ ሰብሳቢዎች ተናገሩ፡፡

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አረዓያ እና ምክትል ሰብሳቢ ሂሩት ገብረስላሴ በህዝብ ጥቆማ ለህዝብ ለመስራት መመረጥ እድል መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር ሰላምና ብልፅግናን ለማረጋገጥም የተሰጣቸውን ሀላፊነት ለመወጣት ″ቁርጠኛ ነን“ ያሉት ዋና ሰብሳቢው ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፥ የልዩነት አጀንዳዎችን ለመጨረሻ ጊዜ ለማረቅ ወሳኝ ምክክር ይደረጋልም ነው ያሉት ።

በአለም አቀፍ ተቋማት ያገለገሉት ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ በበኩላቸው፥ ሁሉንም አሳታፊ በሆነ ውይይት ለአመታት የዘለቁ የፖለቲካ ችግሮችና ፈተናዎችን በመግባባት ለመስራት ዝግጁ ነን ብለዋል።

ከጥቆማ ጀምሮ የነቃ ተሳትፎ ያደረገው ህዝብ በቀጣይም የኮሚሽኑ ተግባራት ላይም ሚናውን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

በተለይ ምሁራን ለሀገር የሚበጁ ሀሳቦችን ወደ ጠረጴዛ በማምጣት ከልዩነት ይልቅ የጋራ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በሀይለየሱስ መኮንን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.