Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሁሉም ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲያገኙ አድርጋለች- አምባሳደር መስፍን ቸርነት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በስነ ስርዓቱ ላይ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ( ዩኔስኮ) የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዩሚኮ ዮኮዘኪ እንዳሉት ÷ በዓለማችን ከአሥሩ ህፃናት አራቱ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትምህርታቸውን የመከታተል እድል አያገኙም።

የሰው ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማርና ሌሎች የህይወት መስተጋብሮችን የመከወን መብት አላቸው ያሉት ዳይሬክተሯ፥ የመንግስታቱ ድርጅት ሁሉም ታዳጊ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትምህርት እንዲያገኙ ለማስቻል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው ÷ኢትዮጵያ ራሱን በቻለ ስትራቴጂ በመመራት ሁሉም ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትምህርት እንዲያገኙ አድርጋለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ የቋንቋና የባህል ሃብታም ነች ያሉት ሚኒስትር ደኤታው፥ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ 55 የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች በአገልግሎት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዓለማችን ሰባት ሺ ያህል ቋንቋዎች ይነገራሉ።

በወንደሰን አረጋኸኝ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.