Fana: At a Speed of Life!

ፖለቲካው ሀገርና ህዝብን አስቀድሞ ይጓዝ ዘንድ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያሳየው ፋይዳ ከፍ ያለ ነው – የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የህዳሴ ግድብ አሁን ላይ ኃይል በማመንጨት ያሳየው ተስፋና ፋይዳ ፖለቲካው ሀገርና ህዝብን አስቀድሞ ይጓዝ ዘንድ ጥቅሙ ከፍ ያለ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን ላይ ሃይል ማመንጨት የጀመረዉ የህዳሴዉ ግድብ የአንድነታችን ማሳያ ነዉ ሲሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ግድቡ አሁን ላይ የደረሰበት ደረጃ የባለብዙ ወገን የድል ምዕራፍ ማሳያ እንደሆነ የኢዜማ ዋና ጸሃፊ አቶ አበበ አካሉ እና የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አብዱል ቃድር አደም አብራረተዋል፡፡

በተለይም የግድቡ ፕሮጀክት የነበሩበትን ዝንፈቶችና ችግሮች ለማስተካከል የተለያዩ ጥረቶች የተደረጉ ቢሆንም እሱን ተከትሎ የመጡ የዲፕሎማሲና ሌሎች ጫናዎች ፈታኝ ሆነው እንደቆዩ ፖለቲከኞቹ አውስተዋል፡፡

ፈተናዎቹንና ተግዳሮቶቹን ለመቋቋም በህዝቡ ብሎም በፖለቲከኞች ዘንድ የተስተዋለዉ በጋራና በአንድነት የመቆም አካሄድ በተጨባጭ አገራዊ ውጤት ማምጣቱን ገልጸው፥ ከዚህ ተሞክሮ ብዙ መማር እንደሚቻል ነዉ የፓርቲዎቹ አመራሮች የተናገሩት፡፡

የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ እንዲሁ÷ ፕሮጀክቱ ፖለቲከኞች ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተዉ በአንድ እንዲቆሙ ያደረገ መሆኑን ጠቁመው÷ ቀሪ ስራዎችን በጥንቃቄና በጋራ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቶዎች እና የፖለቲካ ልሂቃኑ ሀገርና ህዝብን ባስቀደመ ራዕይ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ የገለጹት የፖለቲካ ፓረቲ አመራሮቹ÷ ሀገር በምትፈልገን ጉዳይ ሁሉ አንድነታችንን እና ትብብራችንን እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡

በአወል አበራ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.