Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው ከወለጋ የተፈናቀሉ ዜጎች በጊዜያዊነት ሊያርፉበት የሚችል ቦታ እየተመቻቸ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) በፀጥታ ችግር ምክንያት ከወለጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ፍቃድ ላይ ተመስርቶ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና በብሄራዊ አደጋ መከላከልና ስራ አመራር ኮሚሽን በጋራ ተፈናቃዮቹ በጊዜያዊነት የሚያርፉበት ቦታ እየተመቻቸ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሰጠው ማብራሪያ÷ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከወለጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን አስመልክቶ እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው ብሏል፡፡
 
ቢሮው በወለጋ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ በዚህ ሰሞን ከአካባቢው ተፈናቅለው የመጡ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
የከተማ አሰተዳደሩ እነዚህን ዜጎች ወደከተማይቱ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ጊዜያዊ ድጋፎችንና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ሲሰራና ሲወያይ መቆየቱም አመላክቷል፡፡
 
ይህን መሰረት አድረጎ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ ድረስ በጊዜያዊነት ሊቆዩበት ስለሚቸለው ቦታ የከተማ አስተዳደሩ ከተፈናቃዮቹ ጋር ውይይት መድረጉንም ነው የገለጸው፡፡
 
ይህንን ተከትሎም በተፈናቀሉት ዜጎች ፍቃድ ላይ ተመስርቶ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና በብሄራዊ አደጋ መከላከልና ስራ አመራር ኮሚሽን በጋራ ተፈናቃዮቹ በጊዜያዊነት ሊያርፉበት የሚችል ቦታ እየተመቻቸ ይገኛል ብሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.