Fana: At a Speed of Life!

ለነባር እና አዳዲስ አምባሳደሮች ሥልጠና መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለነባር እና አዳዲስ አምባሳደሮች ለ15 ቀን የሚቆይ ሥልጠና በቢሾፍቱ ከተማ እየተሰጠ ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚሰጠው ስልጠና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ፥ አምባሳደርነት በውጭ ግንኙነት አገልግሎት መስክ የሃገር ብሄራዊ ጥቅሞችን በተቀባይ ሃገር ውስጥ እንዲያረጋግጡ ለማድረግ የህዝብና የመንግስትን ሃላፊነት እና ተልዕኮ የሚወሰድበት የስልጣን ዕርከን ነው ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ባለፉት ጊዜያት የተካሄዱ የለውጥ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ ለስድስት ወራት ወቅቱ የሚጠይቀውን የሀገርን እና ዓለም አቀፍ ሁኔታን መሰረት ያደረገ የአደረጃጀት እና የአሰራር ዘይቤዎች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

በዚህም ከሚሲዮኖች ጋር በጥብቅ በማስተሳሰር የሚፈለገውን ብሄራዊ ለውጥ ማምጣት እንደሆነም አብራርተዋል።

በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ የሚታዩ አዳዲስ እውነታዎችን የሀገርን ወቅታዊ ፍላጎት እና የጂኦፖለቲካ ለውጦች እንዲሁም ከተለምዷዊ የዲፕሎማሲያ አሰራር ጎን ለጎን የዘመኑን ቴክኖሎጂ ያፈራቸውን ውጤቶች በመጠቀም የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ማካሄድ እና የዲጂታል ዲፖሎማሲን በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ማዋልን ታሳቢ አድርጓል ብለዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ያለችበት ቀጠና የበርካታ ባለፀጋ ሀገራት ዐይን ማረፊያ እና የብሄራዊ ጥቅማቸው ሁነኛ ማዕከል ጂኦፖለቲካዊ አካባቢ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

በሌላ በኩል የዓለም ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ ዓለም አሁን ያለበትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት መከተል አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ‘‘አምባሳደሮች የተሰጣችሁን ሃላፊነት በሚገባ መወጣት ይኖርባቸኋል’’ ብለዋል።

ስልጠናው ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ግንኙነት፣ የዲፕሎማሲ ፕሮቶኮል እና ስነምግባር፣ ሃገር በቀል ኢኮኖሚ እና የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ነባር አምባሳደሮች ከአዳዲስ አምባሳደሮችም የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ተብሏል።

በምንይችል አዘዘው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.