Fana: At a Speed of Life!

”ዓድዋስ” ቴአትር የካቲት 22 ለእይታ ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ዓድዋስ” ቴአትር የካቲት 22 በዓድዋ ድል በዓል ዋዜማ ለእይታ ሊቀርብ እንደሆነ የትያትሩ አዘጋጆች ገለጹ፡፡

የቴአትሩ አዘጋጆች ዛሬ ጉዳዩን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የተውኔቱ አዘጋጅ ረዳትፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ ስለ ዓድዋ ከዚህ በፊት ብዙ የጥበብ ስራዎች ቢኖሩም የታሪኩን ያክል ግን ገና አልተሰራም ብለዋል።

የ”ዓድዋስ” ቴአትር ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ወደ ስራ ገብቶ ለእይታ ሊበቃ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል።

ዓድዋ ካለው ውቅያኖስ ከሆነ ታሪክ አንጻር ያንን ሊያሳይ በሚችል መልኩ በአዲስ ቅርጽ ለመስራት ተሟክሯልም ነው የተባለው።

ፀሐፊ ተውኔቱ ያሬድ ሹመቴ በበኩሉ ፥ በአጭር ጊዜ ትልቅ ስራ መስራት መቻሉን ገልጿል።

ለትያትሩ ዝግጅት የሚውል ድጋፍ አድርገዋል ያላቸውን የጥንታዊት የኢትዮጵያ አርበኞች መህበርን አመስግግኗል።

በቴአትሩ በኬሮግራፈርነት የተሳተፈው ተመስገን መለሰ ዓድዋን እስካሁን ባላየነው መልኩ ለማሳየት ተሞክሯል ብሏል።

ቴአትሩ በአብዛኛው በግጥም መልክ የተጻፈ ሲሆን ፥ ሃሳቡን በዳንስና በሰርከስ ለመግለጽ መሞከሩንም ገልጿል።

በቴአትሩ ላይ አበበ ባልቻ፣ ተፈሪ አለሙ፣ ትግስት ግርማና ሌሎች ከ350 በላይ አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል።

ፀሐፊ ተውኔቱ ያሬድ ሹመቴን ጨምሮ፣ ረ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ አዘጋጅ በመሆን፣ ኢዩኤል መንግስቱ በሙዚቃ ድርሰት፣ ተመስገን በኬሮግራፊ እንዲሁም የተመስገን ልጆች በዳንስ እና ሰርከስ ተሳትፈዋል።

ቴአትሩ በዓድዋ በዓል ዋዜማ የካቲት 22 ምሽት 12 ሰዓት በወዳጅነት አደባባይ ለዕይታ እንደሚቀርብም አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

በዘመን በየነ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.