Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ጉዳት ለመቀነስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሰራ ነው – ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ጉዳት ለመቀነስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ሚኒስትሯ በቦረና ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ጉዳት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት እንዲሁም የዓለም ጤና ድርጅትና የዩኒሴፍ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በዚህም ወቅት አርብቶ አደሮቹ የድርቁ ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ነው የጠየቁት።

የተከሰተውን ድርቅ ጉዳት ለመከላከል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ከጤና አንጻር በድርቁ ምክንያት ጉዳቱ ከእንስሳት ወደ ሰዎች እንዳይሸጋገር ይሰራል ነው ያሉት።

“የመከላከልና ምላሽ የመሥጠት ሥራዎችን እንከውናለን፣ የአልሚ ምግብና የሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ላይም እንሰራለን” ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት 31 ሚሊየን ብር የሚገመት የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ አድርጓል።

የዓለም የእርሻና የምግብ ድርጅት “ፋኦ” በአካባቢው የተቀነባበረ የእንስሳት መኖ ማቅረብ መጀመሩ ተመልክቷል።

ድርቁን ለመከላከል ለእናቶችና ሕጻናት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዩኒሴፍ በኢትዮጵያ ተወካይ ጃን ፍራንኮ ሮትግሊያኖ ተናግረዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩና ታሪኩ ለገሰ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.