Fana: At a Speed of Life!

ለቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ት/ ቤት የቤተ ሙከራ ዕቃዎችን ለማሟላት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ለሆነው የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ትምህርት ቤት፣ የቤተ ሙከራ እቃዎችን የማሟላት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና “ስቴም ፓወር” ለቡራዩ ልዩ ተሰጥኦና ተውህቦ ትምህርት ቤት ግንባታ የቤተ-ሙከራ እቃዎችን ለማሟላት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦና ተውህቦ ትምህርት ቤትን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ በሂሳብ እና በኢንጂነሪንግ ዘርፍ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት እንዲሁም የቤተ ሙከራ እቃዎችን የሚገጥም የባለሙያ እቅርቦትን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ለሁሉም ልዩ ችሎታ ያላቸው ኢትዮጵያውያን መፍለቂያ ታስቦ እየተገነባ ያለው ፕሮጀክቱ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ ተናግረዋል፡፡
ከግንባታው መጠናቀቅ ጎን ለጎን የቤተ ሙከራ መሳሪያዎችን የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን የተቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው ÷ ስቴም ፓወር እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የስቴም ፓወር የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ስሜነው ቀስቅስ በበኩላቸው÷ ለቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ትምህርት ቤት የቤተ ሙከራ መሳሪያዎችን እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የቤተ ሙከራ እቃዎችን ብቻ ሳይሆን መሳሪያዎቹን የሚገጠም የባለሞያ ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አንስተዋል፡፡
“ስቴም ፓወር” ሁለት የቤተ-ሙከራ ክፍሎችን ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን የማደራጀት ስራ ለመስራት ስምምነት መደረሱን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.