Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተቋማት የአሰራር ግልጽነትና ገለልተኝነት በተግባር እየተረጋገጠ መጥቷል – ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተቋማት የአሰራር ግልጽነትና ገለልተኝነት በተግባር እየተረጋገጠ መምጣቱን በጠቅላይ ሚኒስትር ዕህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ።

ዶክተር ቢቂላ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ እስካሁን ነጻና ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መፍጠር፣ ጠንካራ ምርጫ ቦርድ ማደራጀትና የፍትህ ስርዓቱን የማሻሻል ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

በተለይም በሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኩል ነፃና ገለልተኛ ተቋም የመፍጠር ተግባር እውን በመሆኑ “ለማመን የሚከብዱ” ሪፖርቶች እየወጡ ይገኛሉ ነው ያሉት።

የኮሚሽኑ ሪፖርት ላይ መንግስት የራሱ እይታ ቢኖረውም ለዜጎች መብት መከበር ግን ተስፋ ሰጭ ክንውኖች መታየታቸውን ገልጸው÷ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

ሌላው የዴሞክራሲ ስርዓት ከሚጠናከርበት መንገድ አንዱ ነጻ፣ ገለልተኛና ፍትሓዊ የምርጫ ስርዓት መሆኑን የተቀሱት ዶ/ር ቢቂላ ÷ በመሆኑም ቦርዱ ከሌሎች አካላት የፖለቲካ ፍላጎትና ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆኖ የአገሪቷን የምርጫ ሂደት እየመራ ይገኛል ብለዋል።

በእነዚህና ሌሎችም ተጨምረውበት በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተቋማት የአሰራር ግልጽነትና ገለልተኝነት በተግባር እየተረጋገጠ መምጣቱን ገልጸዋል።

የፍትህ ተቋማትም ነጻና ገለልተኛ ሆነው ዜጎችን እንዲያገለግሉ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

አሁን በተጀመረው መልኩ የፍትህ ዘርፍ ማሻሻያው ቀጥሎ በኢትዮጵያ ዘላቂና እውነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት እውን ይሆናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.