Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ የአገራችንን ዕጣ ፋንታ ከሚውስኑ ፕሮጀክቶች ትልቁ ነው- አቶ ጃንጥራር ዓባይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የወደፊት የአገራችን ኢኮኖሚ ልማት ዕጣ ፋንታ ከሚወስኑ ፕሮጀክቶች አንዱ እና ትልቁ ይሆናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡
ግድቡ በሙሉ አቅም ወደ ሥራ ሲገባ የሚመነጨው ኃይል ኢንዱስትሪዎችን በማነቃቃት፣ ዜጎች ኃይል እንዲያገኙ በማድረግ እና ለሌሎች አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸጥ የኢኮኖሚ ምንጭ መሆን ሲጀምር ትልቅ አገራዊ ፋይዳ እንደሚፈጠርም ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል፡፡
ግድቡ የአገራችን ኢኮኖሚ ልማት ዕጣ ፋንታ ከሚወስኑ ፕሮጀክቶች አንዱና ትልቁ እንደሚሆን ጠቁመው ፥ በቀጣይ ግድቡ ተጠናቆ የሚፈጠረው የቱሪዝም እንቅስቃሴና እንደ አገር የሚፈጥረው የኢኮኖሚ ልማት ፋይዳ ሲታይ ትልቅ ትርጉም የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁማ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምር ማድረጓ ትልቅ ኩራት ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር ፥ ግድቡ ብርሃን መስጠት መጀመሩም ከፍተኛ ደስታ የሚሰጥና ቀጣይ ለሚደረጉ ሕዝባዊ ድጋፎች መነሳሳት ይፈጥራል ብለዋል፡፡
የአገሪቱ የለውጥ አመራሮች ወደ ሥራ ከገቡበትና የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ ስልት ከተነደፈበት እንዲሁም ማስተካከያ ከተደረገበት ጊዜ ወዲህ ትልቅ መነሳሳት ተፈጥሯል ያሉት ምክትል ከንቲባው÷ ሕዝቡም ባለፈው ዓመት ሁለት ቢሊየን ብር ቦንድ ገዝቷል ብለዋል::
በዚህ ዓመት ለአገሪቱ ሠላምና መረጋጋት ቅድሚያ በመስጠቱ እንዲሁም በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በማገዝ፣ ለክልሎች ድጋፍ በማድረግ ላይ ትልቅ ትኩረት ቢሰጥም ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ማድረጉ እንደቀጠለ መሆኑን አስታውቀዋል::
ከተማ አስተዳደሩ ለግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ያለውን ድጋፍና አስተዋፅኦ አጠናክሮ የሚቀጥልና በሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ለዚህ ሥራ ሌት ተቀን የሚተጋ መሆኑንም ምክትል ከንቲባው ለኢፕድ ገልጸዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ግንባታው 84 በመቶ የደረሰ ሲሆን ፥ እስካሁን ለግድቡ የተደረገ ወጪ 163 ቢሊየን ብርና የግድቡ አጠቃላይ የማመንጨት አቅምም 5150 ሜጋ ዋት መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.