Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋን የምሥራቅ ኢንዱስትሪ ኮሪደር ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማን የምሥራቅ የኢንዱስትሪ ኮሪደር ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸው ተገለጸ፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ያለመ የንቅናቄ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂጿል፡፡
ኢንዱስትሪዎች ከሥራ እድል ፈጠራ፣ ከቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የውጭ ምንዛሬን ከማስቀረት አንጻር ሊጫወቱት የሚገባው ሚና የጎላ እንዲሆን ቢጠበቅም ፥ በተለያዩ ምክንያቶች ውጤታማ አለመሆናቸውን የኢንዱስትሪ ምኒስትር ደኤታ አቶ ሺሰማህ ገብረስላሴ ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታትና የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማድረግ የሚያስችሉ ሂደት ላይ በማተኮር እየገጠሙ ያሉ የፋይናንስ፣ የገበያና የአቅም ግንባታ ክፍተቶችን በመለየት ድጋፍ ይደረጋልም ነው ያሉት።
በድሬዳዋ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለአገር ኢኮኖሚ እያበረከተ ካለው ከፍተኛ ሚና ውስጥ ለበርካቶች የሥራ እድል አየፈጠረ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃርቢ ቡህ ናቸው፡፡
በአስተዳደሩና በመንግስት ትብብር በተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች የኢንዱስትሪው ዘርፍ እያደገና የምርት መጠንና ዓይነት እንዲሁም ብዛት እየጨመረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ድሬዳዋ ለጅቡቲ ወደብ ቅርብ መሆኗ፣የአየርና የየብስ ትራንስፖርት ከሞላ ጎደል የተሟላ መሆኑና ሌሎች መሠረተ ልማቶች በበቂ መጠን እንደመገኘታቸው ለዘርፉ ምቹና ተመራጭ ያደርጋታልም ብለዋል፡፡
በመድረኩ በድሬዳዋ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን የሚመለከት የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት መደረጉን ከከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.