Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ ዛሬ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ተነግሯል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሰያ ትናንት በዩክሬን የጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ መቀጠሉ ተገለፀ።

ዛሬ በሁለተኛ ቀኑም በዩክሬን ርእሰ መዲና ኪየቭ ከባድ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ነው የተነገረው።

በከተማዋ ላይ ሩሲያ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ሰንዝራለች ስትል ዩክሬን ከሳለች።

በእስካሁኑ የግጭቱ ሂደት ሩሲያ የኒውክሌር ማዕከል የሆነችውን ቼርኖቤልን እና በኪየቭ አቅራቢያ የሚገኝ የዓየር ሀይል ማዘዣን መያዟ ነው የተነገረው። ትናንትናም 74 ወታደራዊ ተቋማትን ማውደሟን ሞስኮ ገልፃ ነበር።

በሌላ በኩል የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜነልሰኪ ከሩሲያ ጋር ሀገራቸው ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

ምዕራባውያን ከጎናቸው መሆናቸው እንደነገሯቸው የገለጹት ቮሎድሚር ዜነልስኪ ÷ ነገር ግን ኔቶም ሆነ ምዕራባውያን ተግባራዊ ድጋፍ ሊያደርጉላቸው አለመፍቀዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ከየአውሮፓ ሀገራት ድጋፍ እንዲደረግላቸው የፈለጉት ፕሬዚዳንቱ ከ27 መሪዎች ጋር ቢወያዩም ሁሉም ፈርተው ምላሽ ሊሰጧቸው አለመቻላቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም ዩክሬን ገለልተኛ በሆነ መንገድ ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ጠቁመው÷ ይህን ለማድረግም የሶስተኛ ወገን ዋስትና እንደሚያስፈልግ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን እንቅስቃሴ መጀመሯን ተከትሎ በሞስኮ እና ኬይቭ መካከል ውጥረት ተፈጥሯል።

በተለይም ሩሲያ ለሁለት ተገንጣይ የዩክሬን ግዛቶች እውቅና መስጠቷ ችግሩን ይበልጥ አወሳስቦታል ነው የሚባለው፡፡

ቻይና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል እንደገለፀችው፥ ቤጂንግ ሩሲያ የምታነሳቸውን የደህንነት ስጋቶች ትረዳለች። በሌላ በኩል ደግሞ ለሁሉም ሀገር የግዛት ሉዓላዊነት እውቅና ትሰጣለች።

በመሆኑም ሁሉም ወገን ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት አስተሳሰብ በመላቀቅ በድርድር ዘላቂ ለሆነ የአውሮፓ ሰላምና ፀጥታ መስራት እንደሚገባ ማመልከቷን ከቲ አር ቲ እና ሲ ጂ ቲ ኤን ያገኘናቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.