Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ወጣቶች አቀባበል አደረገ

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ወጣቶች በፍቼ ከተማ አቀባበልና የምሳ ግብዣ አድርጎላቸዋል።

የወልቃይት ወጣቶች ኦሮሚያ ክልል ፍቼ ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች እና አባገዳዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበልና የምሳ ግብዣም አድርገውላቸዋል።

ወንድም የአማራ ህዝብ “የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው” ብሎ ግንባሩን ለጥይት የሰጠው በለውጡም ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አብሮ ከጎኑ የቆመ መሆኑ በዚሁ አቀባበል ላይ ተነስቷል።

ወጣቶቹ በአማራ ክልል በጎንደርና ጎጃም የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው በዛሬው እለት ወደ ሸዋ እያቀኑ ሲሆን የአማራ ወጣቶች በዚህ ሳምንት እየተካሄደ በሚገኘው የታሪካዊ እና የቱሪዝም ስፍራዎች ጉብኝት እና የወንድማማችነት መርሀ ግብር ደብረ ብርሃን የሚደርሱ ይሆናል፡፡

ደብረ ብረሀን ከተማ ሲደርሱም ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወን ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.