Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እጣ ወጥቶባቸው የነበሩ የ20/80 እና የ40/60 ኮንደሚኒየም ቤቶች ቁልፍ ለባለ ዕድለኞ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤቶች ልማት ፕሮግራም ተገንብተው እጣ የወጣባቸውን የ20/80 እና የ40/60 መኖሪያ ኮንደሚኒየም ቤቶች ቁልፍን ለባለ ዕድለኞች አስረከበ።

የ20/80 ኮንደሚኒየም ቤቶች ተገንብተው ለባለዕድለኞች ሲተላለፉ ይህ ለ13ኛ ጊዜ ሲሆን የ40/60 ኮንደሚኒየም ቤቶች ግንባታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት የተፈጸመው ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አመልክቷል፡፡

ርክክብ የተፈጸመባቸው ቤቶች “ቱሪስት ሳይት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገነቡት እንደሆኑም ተጠቅሷል።

“በቱሪስት ሳይት” የተገነቡት ኮንደሚኒየም ቤቶችም ባለ 11 ወለል ፎቅ እንደሆኑና በአጠቃላይ 1 ሺህ 930 ክፍሎች እንዳላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በቀጣይም ያላለቁ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ለማስረከብ ከተማ አስተዳደሩ እየሠራ መሆኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዋ ያስሚን ዋህብራቢ ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊዋ፥ በአዲስ አበባ የሚስተዋለውን የቤት እጥረት ለመቅረፍም በአቃቂ አካባቢ 5 ሺህ ቤቶች የተጀመሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከ12 ሺህ በላይ ቤት ፈላጊ የከተማዋ ነዋሪዎችም በማኅበር መደራጀታቸው የተጠቆመ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ ችግሩን ለማቃለል እየሠራ መሆንም ተመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.