Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲው የእንቦጭ አረም እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል እየሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የእንቦጭ አረም በውኃ አካላት ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት በጋምቤላ ክልል ጎግ ወረዳ በሚገኘው የታታ ሐይቅ ላይ የእንቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ አካሂደዋል።
የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋልዋክ ጋርኮት እንዳሉት÷ በክልሉ በሚገኙ የውኃ አካላት ላይ የእንቦጭ አረም እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በጉልበትና በምርምር ለማገዝ ዩኒቨርሲቲው እየሠራ ነው።
በሐይቆች፣ ወንዞች እና ኩሬዎች ላይ አረሙ የሚያደርሰውን ጉዳት በጥናት በመለየት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እንደሚሠራም ነው ገልጸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ዶክተር ቾል ኬት በበኩላቸው÷ አረሙን ለማስወገድ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን በምርምር ለማፍለቅ እንደሚሠራ ጠቁመው÷ ከተያዘው በጀት ዓመት ጀምሮ የእንቦጭ አረም ላይ ምርምር ለማካሄድ ተግባራዊ ሥራ ተጀምሯል ብለዋል።
መምህራንን በማሳተፍ ጭምር እንቦጭ አረም ላይ በሚካሄደው ምርምር ተመራቂ ተማሪዎችም ጥናታቸውን በእንቦጭ ላይ እንዲሠሩ እየተደረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የጎግ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡጁሉ ጎራ÷ እንቦጭ አረም በታታ ሐይቅ ላይ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት የሐይቁ መጠነ ስፋት ከ457 ሄክታር ወደ 251 ሄክታር ዝቅ ማለቱን አብራርተዋል፡፡
ሐይቁን ከመጥፋት ለመታደግ የመከላከል ሥራው ውጤታማ እንዲሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትብብር ይጠይቃል ማለታቸውን ማለታቸውን ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.