Fana: At a Speed of Life!

የጾሙ ወቅት ጽንፈኝነትና ዳተኝነት የሚረቱበት፤ ፍቅርና መተሳሰብ የሚበረቱበት እንዲሆን ምኞቴ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጾሙ ወቅት ጽንፈኝነትና ዳተኝነት የሚረቱበት፤ ፍቅርና መተሳሰብ የሚበረቱበት፤ መለያየትና መነቃቀፍ ድል የሚሆኑበት፣ መረዳዳትና መደጋገፍ የሚሠለጥኑበት እንዲሆን ምኞታቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ለዐቢይ ጾም እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

በድርቅና በጦርነት ምክንያት የተቸገሩትን እያሰብንና እየረዳን፤ የተፈናቀሉትን እና የተሰደዱትን እየተቀበልን እንድንጾመው አደራ እላለሁ ብለዋል።

በጾምና በጸሎት ተግተን ሰላምና ብልጽግና የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለማየት ያብቃን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.