Fana: At a Speed of Life!

ለሕዝቦች ባህል ማዕከላት መገንቢያ መስጠት የችሮታ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታችን ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጋምቤላ ባህል ማእከል ግንባታ 5 ሺህ ካ.ሜ ቦታ አስረከበ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት÷ ሁላችንም ባለቤት በመሆናችን ሰብሰብ ብለን መዲናችንን እናሳድግ ብለዋል፡፡ ለህዝቦች ባህል ማእከላት መገንቢያ መስጠት ለኛ የችሮታ ጉዳይ ሳይሆን የግዴታችንም ጭምር ነው ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
መተማመንን በጋራ መልማትን እና ፍትሃዊነትን ልናጎለብት የምንችለው እንዲህ አይነት መገለጫዎችን ስናበረታታና ስናሰፋ ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች÷ አዲስ አበባን የምናሳምረው ፓርኮችን በመገንባት ብቻ ሳይሆን ልጆቿን አንድ ሊያደርግ የሚችል ስራ በመስራት ጭምር ነው በማለት ገልፀዋል፡፡
የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጅሉ በበኩላቸው÷ አዲስ አበባን የሁላችም ቤት የማድረግ ስራ በሁላችንም ላይ ከፍተኛ ኩራት የፈጠረ ተግባር በመሆኑ ለከተማ አስተዳደሩና ለህዝቡ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ የክልላችንን ባህል የምናስተዋውቅበትና ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር በብዙሃነት አንድነታችንን የምናሳይበት እንዲሁም አንድነታችንና ወንድማማችነታችንን በጋራ የምናጎለብትበት ነውም ብለዋል፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያውያንን ከጠረፍ ወደ መሃል የሚያመጣ ትልቅ እርምጃ ነው፤ ሁሉም የሃገሪቱ ህዝቦች በዚህ የኢኮኖሚ ማእከል ከተማ ውስጥ ገብተው የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ መደረግ ይኖርባቸዋል፤ እርምጃውም ይሄን የሚያበረታታ ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.