Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ጉባኤውን ሊያካሂድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ጉባኤውን ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

በጉዳዩ ላይ የብልጽግና ፖርቲ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ እና የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሙፈሪያት ካሚል፣ ብናልፍ አንዷለምና ተስፋዬ በልጂጌ ዛሬ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷ የጉባኤው መሪ ቃል ‘ከፈተና ወደ ልዕልና’ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን÷ በጉባኤው ፖርቲውን በብቃት የሚመሩ አመራሮች ይመረጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የጉባኤው ሰነድና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እየተዘጋጁ መሆኑንም በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው በፓርቲው ጉባኤ 1600 በድምጽና 400 ያለድምጽ የሚሳተፋ ጉባኤተኞች እንደሚኖሩም ነው የተገለጸው።

በጉባኤውም የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ፖለቲከኞችና ከ38 ሀገራት የተወጣጡ የእህት ድርጅቶች ተወካዮች ይታደማሉ።

ከዛሬ ጀምሮም የፖርቲው አባላት ከታች ጀምሮ በየደረጃው ኮንፍረስ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴዎች ባለፉት ቀናት ባደረጓቸው ስብሰባዎች በተለያዩ ወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይተው በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወቃል።

ብልፅግና ፖርቲ ከ11 ሚሊየን በላይ አባላት እንዳሉት ተገልጿል።

በሀይለየሱስ ስዩም

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.