Fana: At a Speed of Life!

የጣሊያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒ ለሦሰት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ምክትል ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፥ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም በጣሊያን አጋርነት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚጎበኙ መሆኑን በኢትዮጵያ ከጣሊያን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ማሪና ሴሬኒ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የሚያደርጉት ውይይትም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ግልጽ መረጃ እንዲኖራቸው ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.