Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማዘመን እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የግብርናውንና የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማዘመን እንዲሁም ለማስተሳሰር በርካታ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው እንደገለጹት÷ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን የበለጠ ውጤታማ በማድረግ የሚያበረክቱትን አስተፅኦ ማሳደግ እንዲችሉ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡
በሚኒስትር ዴኤታዋ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች የሚገኙ የቡልቡላ እና የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝቷል፡፡
በዚሁ ወቅት ሰመሬታ ሰዋሰው እንደገለጹት፥ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ መሉ በመሉ ወደ ስራ ሲገቡ ከሚፈጥሩት የሥራ ዕድል በተጨማሪ አርሶ አደሩ ከተሻለ የአመራረት ዘዴ ጋር እንዲተዋወቅ እንዲሁም ምርቱን ለገበያ በማቅረብ በተሻለ ዋጋ እንዲሸጥ ይረዳል ብለዋል፡፡
መንግሥት ወደ ተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ለሚገቡ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያደረግ ገልጸው፥ በፓርኮች ውስጥ ተቀጥረው ለሚሰሩ ሠራተኞችም የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ ኦሬሊያ ፓትሪዛ በበኩላቸው፥ ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች ከመተካት ባሻገር ጥራት እና ተወዳዳሪ ምርቶችን በማቅረብ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን የገበያ ዕድል ሊጠቀሙ ይገባል ማለታቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.