Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ ከተማ ከ14 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ፍቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ስራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ከ14 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ፍቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዳማ ከተማ የኢንዱስትሪና ኢንቨሰትመንት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በዘርፉ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ በአዳማ ተካሂዷል።

የአዳማ ከተማ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቱራ ግዛው ለኢዜአ እንደገለጹት ፥ ባለፉት ስድስት ወራት በከተማዋ ከ14 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ አግኝተው ወደ ስራ ገብተዋል።

የኢንቨስትመንት ፍቃድ አግኝተው ወደ ስራ የገቡ ባለሃብቶች በተሰማሩባቸው የልማት ዘርፎች ከ44 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ አድል የሚፈጥሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ከ923 ሚሊየን ብር በላይ ከፒታል ያስመዘገቡ አርሶ አደሮች የኢንቨስትመንት ፍቃድ አገኝተው በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰማራታቸውን ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ በአምስት ማህበራት የተደራጁና ከ800 በላይ አባላት ያሏቸው መሆኑን የገለጹት ሃላፊው ፥ በአብዛኛው ወደ ኢንቨስትመንት የተሻገሩ አርሶ አደሮች በራሳቸው መሬት ላይ የሚያለሙ መሆኑን አመልክተዋል።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ በበኩላቸው ፥ “ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ምቹ በማድረግ ለባለሃብቱና ለአርሶ አደሩ በወቅቱ መሬትና የይዞታ መረጋገጫ ካርታ አስረክበን ወደ ስራ እንዲገቡ አድርገናል” ብለዋል።

ወደ አንቨስትመንት ለተሸጋገሩ አርሶ አደሮች እንዲሁም ለባለሃብቶች ከ85 ሄክታር በላይ መሬት መተላለፉን ለአብነት ጠቅሰዋል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.