Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የቀጠናዊ የሠራተኞች ፍልሰት የሚኒስትሮች ፎረምን የመምራት ኃላፊነት ከኬኒያ ተረከበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረም ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለሚቀጥሉት 2 ዓመታት የሚኒስትሮች ፎረምን የመምራት ኃላፊነትን ከኬኒያ መረከቧ ተገለጸ፡፡
የሠራተኞች ፍልሰት አስተዳደርን በማሻሻል ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር ከኬንያ የሰራተኛና ማህበራዊ ዋስትና ሚኒስትር ሲሞን ቼሉጉዊ ጋር ገንቢ ውይይት ማካሄዳቸውን የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገልፀዋል፡፡
ላለፉት 2 ዓመታት በኬንያ የተመራ የ11 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት ቀጠናዊ የሠራተኞች ፍልሰት መማክርት የሚኒስትሮች ፎረም በርካታ ተግባራትን ሲያካሄድ መቆየቱን ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
ለዚህም የመሪነቱን ሚና ለተጨዋተው ኬንያ እና ለፎረሙ አባል ሀገራት ምስጋና ይገባል ብለዋል፡፡
በሀገራት የስራ ገበያ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የሰለጠነ የሰው ሀይል አምርቶ ለገበያ ማቅረብ የሀገራቱን ኢኮኖሚ ከመደገፉም ባሻገር ዜጎች የሚገባቸውን ክብርና ጥቅም እንዲያገኙ ያስችላልም ነው ያሉት።
ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሌሎች ጉዳዮች ሁሉ በዚህ ዘርፍም የተሰጣትን የመሪነት ሚና ቀጠናዊ ትስስሩን ይበልጥ ለማጠናከርና ፈጣን ለውጥ ለማምጣት በትጋት እንደምትሠራም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.