Fana: At a Speed of Life!

በማቻክል ወረዳ በኤሌክትሪክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
 
አደጋው የካቲት 21 ቀን ለ22 አጥቢያ ከሌሊቱ 6 ሰዓት አካባቢ የተፈጠረ ሲሆን÷የአደጋውን መንስኤም ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በተፈጠረው አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ማህበረሰቡ የኤሌክትሪክ ሃይል አጠቃቀሙ ላይ ጥንቃቄ በማድረግ ከመሰል አደጋዎች ራሱን መጠበቅ እንዳለበትም ጥሪ ቀርቧል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.