Fana: At a Speed of Life!

ማዕከሉ በፈጠራ ክህሎት እድል ላጡ ወጣቶችና ሴቶች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትና በጣሊያን መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የተገነባውን የምርት ፈጠራ ማዕከል ጎበኝተዋል፡፡
 
በጉብኝታቸው ወቅት ተቋሙ በተለይ በፈጠራ ክህሎት እድል ላጡ ወጣቶችና ሴቶች ወሳኝ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
 
 
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩ ወልዴ በበኩላቸው÷ ተቋሙ ባለፉት 80 ዓመታት በተለያየ አደረጃጀትና ስያሜ የአገሪቱን አነስተኛ አምራቾች ለመደገፍ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
 
አሁን ላይ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች ታሳቢ ያደረጉ የድጋፍ አማራጮችን በማጠናከር ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል ፡፡
 
በጉብኝት መርሃ ግብሩ የጣሊያን ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒም መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.