Fana: At a Speed of Life!

በቪላ ዲ ማድሪድ የዓለም የቤት ውስጥ ቱር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወርቅ ደረጃ በተሰጠው እና ትላንት ምሽት በስፔን በተካሄደው ቪላ ዲ ማድሪድ የዓለም የቤት ውስጥ ቱር ውድድር ኢትዮጵያያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ድል ቀንቷቸዋል።
በዚህም መሠረት በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ሰለሞን ባረጋ 7:34.03 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸነፊ ሆኗል፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር ለሜቻ ግርማ 7:37.09 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ፣ አዲሱ ይሁኔ ስድስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በተመሳሳይ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ 3:57.38 በሆነ ሰዓት በመግባት የቦታውን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል አሸነፊ ሆናለች፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር ሂሩት መሸሻ 4:02.22 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ 4:03.38 በሆነ ሰዓት በመግባት ሦስተኛ እንዲሁም አክሱማዊት አምባዬ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በሌላ በኩል አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር፣ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በ1 ሺህ 500 ሜትር በ2022 በውድድር ርቀቶቹ በቱሩ ባስመዘገቡት ድምር ውጤት ቤልግሬድ ለሚደረገው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በቀጥታ ተሰላፊ የመሆን እድል ማግኘታቸው ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.