Fana: At a Speed of Life!

የእናቶችን ጤና ለማሻሻል እየሰሩ ላሉ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእናቶችን ጤና ለማሻሻል ከጤና ሚኒስቴር ጋር እየሰሩ ላሉ አጋር አካላት የእውቅና እና የምስጋና መርሀ ግብር ተካሔደ።
በምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የእናቶች እና ህጻናት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም ፥ የጤናማ እናትነት ወርን በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶች፣ ለእናቶች ጤና ጠቃሚ በሆኑ ተግባራት እንዲሁም በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የጤና አገልግሎቱ መነቃቃት መፈጠር የሚያስችሉ ድጋፎችን በማቅረብ ሲከበር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ለዚህ ስኬት ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን እና ጊዜያቸውን ላበረከቱ እንዲሁም በእናቶች ጤና ዙሪያ ትልቅ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም በእናቶች ጤና ዙሪያ ትልቅ ርብርብ እና ጥረት እንደሚያስፈልግ ገልፀው ፥ አጋር አካላትም የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስክር ወረቀት መሰጠቱም ተገልጿል፡፡
“በማንኛውም ሁኔታ ከወሊድ በኋላ በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶችን ሞት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንግታ” በሚል መሪ ቃል በአለም ለ35ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የጤናማ እናትነት ወር መከበሩን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.