Fana: At a Speed of Life!

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ጉዳዮች የሚመክረው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ÷ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ ስለሚገኙ አመራሮች እና አባሎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ቦርዱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ምላሹን የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሜዴቅሳ እና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ናቸው፡፡
የቦርዱ አመራሮች እንደገለጹት÷ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት እና አመራሮች ላይ ያለ ፍርድ ቤት ዕውቅና ስለታሰሩ አመራሮች እና አባሎቻቸው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን የሚያጣራ የሶስትዮሽ ቡድን አቋቁሞ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቷል።
ከምርጫ ቦርድ፣ ገዥው ፓርቲ እና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች የተቋቋመው አጣሪ ቡድንም በተለያዩ ክልሎች ምልከታ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በዚህም መሠረት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታሰሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት መታሰራቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷ ጉዳዩ ሲጣራ ቆይቶ አብዛኞቹ እስረኞች እየተፈቱ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡
እንደ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ገለጻ÷ አሁንም እስረኞች በየ ማረሚያ ቤቱ እና ፖሊስ ጣቢያው መኖራቸውን ጠቁመው÷ በቁም እስረኝነት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እንዳሉበትም ተናግረዋል፡፡
ይህም ከሕግ ሂደት እና አሰራር ውጭ በመሆኑ÷ መንግስት አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ በቁጥጥ ስር የሚገኙ እስረኞች እንዲፈቱ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ብሄራዊ የመረጃ እና ደህንነት ጋር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
በአንዳንድ አካባቢ ዎች ስለሚገኙ እስረኞች ዕውቅና የለንም የሚሉ አመራሮች መኖራቸውን ገልጸው÷ ለዚህም አስቸኳይ እልባት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የመድብለ ፓርቲ ግንባታ፣ በምርጫ እና ምርጫ ነክ ጉዳዮች፣ በሕገ መንግሰታዊ ጉዳዮች፣ የሀገረ መንግስት ምስረታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።
በምንይችል አዘዘው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.