Fana: At a Speed of Life!

በዩክሬን ቀውስ ውስጥ ሁሉም ወገኖች ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣የካቲት 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በዩክሬን ቀውስ ውስጥ ሁሉም ወገኖች ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠየቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዩክሬን የተፈጠረውን ቀውስ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ በቅርቡ ካለፈችበት ጦርነት ተነስታ ስለ ጦርነት ጉዳት የምታካፍለው ሰፊ ልምድ እንዳላት አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ልምድ ጦርነት ቤተሰብን፣ ማህበረሰብን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ ክፉኛ የሚጎዳ፣ አጥፊ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ጦርነት የሚያደርሰውን ቁሳዊ ጉዳት መጠገን ቢቻልም በማህበረሰብ ላይ ጥሎት የሚያልፈውን ጠባሳ ግን ለማከም ከባድ መሆኑን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ወቅታዊውን የዩክሬን ቀውስ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ግጭቱን የሚያባብሱ ሁኔታዎች እንደሚያሳስባት ነው ያመለከቱት።
በመሆኑም ሁሉም ወገኖች ቀውስን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅበው ግጭቱን ለመፍታት ሁለንተናዊ የሰላም መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል። አክለውም በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ያላቸውን ምኞት ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.