Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲው የኢትዮ-ሱዳንን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ለማጠናከር እየሠራሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮ-ሱዳንን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ለማጠናከር ከሱዳን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡
የሱዳን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በሱዳን ከአምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ጋር የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ÷ የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ለማጠናከር የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አምባሳደር ይበልጣል ገልጸዋል፡፡
የሱዳን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጎንደር እና ባህርዳር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ መስራታቸው አበረታች መሆኑን ጠቅሰው÷ የጋራ ታሪካዊና ባህላዊ ዕሴቶችን የሚያጎለብት ኩነቶችን በማዘጋጀት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን ይበልጥ ለማጠናከር መሥራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የሱዳን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በበኩላቸው÷ የሁለቱን ሕዝቦች ትስስር ለማጠናከር ባላቸው እውቀትና ልምድ ከጎንደርና ባህርዳር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቅርቡም በካርቱም የጋራ መድረክ ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ጠቁመው÷ በቀጣይ የሁለቱን ሀገራ ሕዝቦች ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት የቻሉትን ሁሉ አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.