Fana: At a Speed of Life!

የቱርኩ ኤም ጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎቱን አሳወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲ) በበርካታ አገሮች ውስጥ አምራች ፋብሪካዎች ያሉት የቱርኩ የኤም. ጂ.ፕሮጀክቶች ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ያለውን ፍላጎት ማሳየቱን በአንካራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
የኤም ጂ ፕሮጀክቶች ፕሬዚዳንት ሚስተር ጆርጂ ሀድድና ባልደረቦቻቸው ከኤምባሲው ጋር ባደረጉት ውይይት፥ በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለማወቅ የቅድመ ዝግጅት ጉብኝት በማድረግ በተለይም በወረቀት ማምረት፣ በህክምና እና በኃይል አቅርቦት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀዋል።
በውይይቱም÷ በቱርክ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሀመድ÷ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ምቹ ሁኔታዎች እንዲሁም መንግሥት ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ዘርፎች ገለጻ አድርገዋል።
የኤም ጂ ፕሮጀክቶች በኃይል አቅርቦት፣ በህክምናው ፣ በቤት ቁሳቁስ ምርት፣ በወረቀት እና ሌሎች ዘርፎች በመሳተፍ በሊባኖስ ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች፣ አሜሪካ ፣ ካናዳ እና ቱርክ ላይ በርካታ ፋብሪካዎች ያሉት ግዙፍ ኩባንያ ነው።
ኩባንያው በቀጣይ በኢትዮጵያ ለሚያደርገው ጉብኝት እና የሥራ እንቅስቃሴ ሚሲዮኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል መባሉን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.