Fana: At a Speed of Life!

በጉምቢ ቦርዶዴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በጉምቢ ቦርዶዴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 3 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በወረዳው የትራፊክ አስተባባሪ ዋና ሳጅን ኡመር ኡስማን ገለጹ፡፡
በአደጋው በ23 ሰዎች ላይም ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ “ቦቴ” የፈሳሽ ጭነት ተሽከርካሪ ከጭሮ ወደ አዳማ ሲጓዝ ከነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር ተጋጭተው መሆኑንም ነው ዋና ሳጅን ጨምረው የገለጹት፡፡
የአደጋው መንስኤ በጥንቃቄ ጉድለት ማሽከርከር መሆኑንም ገልጸው÷ የፈሳሽ ጭነት ተሸከርካሪው መስመሩን ስቶ ወደ ሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው መስመር በመግባቱ በተከሰተ ግጭት መሆኑን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.