Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል የበጋ ስንዴ ምርት የመሰብሰብ ተግባር ሁምቦ ወረዳ በይፋ ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በዘንድሮው በጋ በመስኖ የለማ የቆላ ስንዴ ምርት መሰብሰብ ተግባር በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ አምፖ ኮይሻ ቀበሌ በይፋ ዛሬ ተጀምሯል።

በክልሉ የለማው የቆላ ስንዴ በሦስት ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ዝግጁ መሆኑን የግብርና ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ክልል በተያዘው የበጋ ወቅት በበጋ መስኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ የተሸፈነ ሲሆን÷ የግብርና ባለሙያዎች እንዳሉትም የለማው የቆላ ስንዴ በሦስት ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ዝግጁ ሆኗል።

መረሃ ግብሩም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ አምፖ ኮይሻ ቀበሌ በኤላ መስኖ የለማ 97 ሄክታር ማሳ ላይ መጀመሩን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመርሀ ግብሩ በደቡብ ክልል መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮው ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፓለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማና ሌሎችም አመራሮች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.