Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትረያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት መጋቢት 4 ቀን ይፈጸማል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትረያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመጪው መጋቢት 4 ቀን ይፈጸማል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል መጋቢት 4 ቀን እንደሚፈጸም ቅዱስ ሲኖዶሱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ መወሰኑን፥ የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን እስክንድር ገብረክርስቶስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ቀደም ብሎ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው የፊታችን እሁድ እንዲፈጸም ተወስኖ የነበረ ቢሆንም፥ በውጭ አገራት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸውና የተለያዩ አገራት የሃይማኖት መሪዎች በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ እንዲገኙ በማሰብ መጋቢት 4 ቀን እንዲፈጸም መወሰኑ ታውቋል።

ቅዱስነታቸው በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ምሽቱን ማረፋቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.