Fana: At a Speed of Life!

ኢዜአ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡
 
በአከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዜናዎችን ሰንዶ የመዘገብ ልማድ ያላቸው ዘላቂና አገር አሻጋሪ ተቋማትን መደገፍ እና ማላቅ ያስፈልጋል ብለዋል።
 
ኢዜአ በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎችን በማፍራት ለኢትዮጵያ የሚዲያ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ አንጋፋ ተቋም መሆኑንም ገልጸዋል።
 
ኢዜአ ያለውን የበርካታ ዓመታት ልምድ ተጠቅሞ ታሪክ የመሰነድ ስራውን እንዲወጣም አሳስበዋል።
 
የምስረታ በዓሉ በፎቶ ዓውደ ርዕይ፣ በፓናል ውይይት እና በሌሎች መርሃ ግብሮች ነው የሚከበረው።
 
በፈትያ አብደላ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.